/ሙላት

Published

- 2 min read

/ኢኮቱሪዝም ምንድን ንው?

img of /ኢኮቱሪዝም ምንድን ንው?

/ኢኮቱሪዝም ቱሪስቶች አካባቢን በሚጠብቅ, የአካባቢውን ሰዎች ደህንነት በሚጠብቅ ሁኔታ እንዲጎበኙ የሚያደርግ ስርአት ነው. የ ዓለም አቀፍ የኢኮቱሪዝም ማህበር እ.ኤ.አ. በ 2015 (TIES, 2015) ኢኮቱሪዝምን “አካባቢን የሚንከባከቡ ፣የአካባቢውን ህዝብ ደህንነት የሚደግፉ እና ትርጓሜ እና ትምህርትን ወደሚያሳድጉ የተፈጥሮ አካባቢዎች ኃላፊነት ያለው ጉዞ” ሲል ገልጿል። 

/የኢኮቱሪዝም ትልቅ ምሳሌ የሆነው የወንጪ-ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት ተመረቀ. መደመር በተግባር የታየበትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ስራ መስራት እንደሚቻል የተረጋገጠበት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ /ድር. አብይ /አሕመድ ገለጹ።

/ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጪ-ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክትን ዛሬ ሲመርቁ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ ከተለያየ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተሰባሰበ ሀብት፣ ከተለያዩ አካባቢዎች በመጡ ባለሙያዎች እና የፕሮጀክት አስተባባሪዎች የተገነባና መደመር በተግባር የታየበት ነው ብለዋል። ከወንጪ አካባቢ የወጡ በርካታ ጀግኖች የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅና ሉዓላዊነት ለማስከበር ትልቅ ውለታ መዋላቸውን አስታውሰዋል። መደመር በጋራ ተያይዞ ማደግ መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መደመር ወሳኝ ነው ብለዋል።

/ፕሮጀክቱ ወንጪንና አካባቢውን በልማት ማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። የወንጪ-ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ያቀፈ በመሆኑ ባለሀብቶች በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል። የወንጪ-ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት ስራን ጀምረን በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ማከናወን እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል።

/ይህ ፕሮጀክት ጅምር ስራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ አምቦን፣ ወንጪ-ደንዲ ሀይቅን፣ ወሊሶን አንድ ላይ የሚያስተሳስር ትልቅ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ለዚህም ባለሀብቶች በስፋት በኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ የክልሉ መንግስት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

/የወንጪ አካባቢ ማህበረሰብ የአካባቢውን ተፈጥሮ ጠብቆ እንዳቆየ አሁንም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል። በባህሉ እንግዳ ተቀባይ የሆነው ህዝብ ወንጪ-ደንዲን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶችን ተንከባክቦ አስተናግዶ በደስታ እንዲመለሱ በማድረግ የጎብኚዎችን ቀልብ መሳብና የተሻለ ገቢ የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርበታል ብለዋል።