/ሙላት

Published

- 3 min read

/የህዳሴ /ግድብ /ወደ /ማጠናቀቂያ /ምዕራፍ /ተሻገረ

img of /የህዳሴ /ግድብ /ወደ /ማጠናቀቂያ /ምዕራፍ /ተሻገረ

/ታላቁ የ /ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ብርቱ ጥረትና ፅናት ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ መሸጋገሩን የግድቡ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ገለጸ። ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ትስስር እና ለጋራ ልማት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተገልጿል።

/ህዝቡ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት እስከ ህዳር 30/2016 ድረስ ባሉት ዓመታት ከ18 ቢሊዮን 734 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በስብሰባውም የ2015 አፈጻጸም፣ የ2016 እቅድና ያለፉት አምስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል። በግምገማውም የህዝብ ተሳትፎ፣ የተፋሰስ ልማት፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የፋይናንስ ድጋፍን የተመለከቱ ጉዳዮች ተዳስሰዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር /ደመቀ /መኮንን

/የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር /ደመቀ /መኮንን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 12 ዓመታት በፅናት ገንዘቡን፣ እውቀቱንና ሙያውን ለግድቡ ግንባታ በማዋል ቃሉን በተግባር በመፈጸም ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ማሸጋገሩን ተናግረዋል። የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 94 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን ገልጸው፤ ህዝቡ ያለመታከት ድጋፍ በማድረግ፣ የተፋሰስ ጥበቃ ስራ በመስራት የይቻላልን መንፈስ ለዓለም ማሳየቱን ተናግረዋል።

/ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የአብሮነትና ሀገር ወዳድነት ቋሚ መገለጫ እንደሆነም ነው /አቶ /ደመቀ ያስረዱት። በመሆኑም በቀጣይ ህዝቡ በልዩ ልዩ መስክ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ መቀመጡን አብራርተዋል።

/ጠቅላይ ሚኒስትር /ዶር. አቢይ /አሕመድ እና የግብጹ ፕሬዝዳንት /አብዱል /ፋታህ /አልሲሲ የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር እንዲጀመር ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ባለፉት ወራት አራት ዙር ድርድሮች መካሄዳቸውን አውስተዋል። በዚህም በብዙ ጉዳዮች መግባባት ላይ ቢደረስም በዋና የልዩነት ነጥብ ላይ አሁንም መግባባት አለመደረሱን ተናግረዋል።

/ግብፅ የሶስትዮሽ ድርድሩ አያስፈልግም የሚል አቋም ይዛ በመውጣቷ ድርድር መቋረጡንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ድርድሩ መርህን በተከተለ መንገድ እንዲካሄድና መግባባት ላይ እንዲደረስ አሁንም ቁርጠኛ ናት ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለቀጣናዊ ትስስር እና ለጋራ ልማት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

/በውይይቱ የተሳተፉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ግድቡን በተሳካ መንገድ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ የዘርፍ ተቋማትና ክልሎች በልዩ ቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የኮሚቴው አባልና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፥ ባለፉት አምስት ወራት ለግድቡ ግንባታ የተደረገው የሀብት ማሰባሰብ ስራ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየቱን ገልጸዋል።

/የግድቡ የሲቪል ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህ ዓመትም ተጨማሪ ተርባይኖችን ወደ ኃይል ማመንጨት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

/ሌላኛው የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባልና የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፤ በስብሰባው ከተቀመጡት አቅጣጫዎች አንዱ የግድቡን አካባቢያዊ ደህንነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል።

/በመሆኑም ግድቡ ተጠናቅቆ ወደ ሙሉ ስራ ሲገባ ለረጅም ዓመታት ደህንነቱ ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጥ፣ ወደ ግድቡም የተጣራ ውሃ እንዲገባና ደለል እንዳይከማች መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል። ለዚህም የግብርና ሚኒስቴር የሚያስተባብረው ኮሚቴ የዓባይ ተፋሰስ የአረንጓዴ ልማትን ከሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ጋር አስትሳስሮ ይሰራል ነው ያሉት።

/በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስበሰባ የግድቡ ግንባታ የተጀመረበት 13ኛ ዓመት በዓል ኢትዮጵያውያን ቃላቸውን በተግባር ያጸኑበትን አውድ በሚገልፅ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል። በውጭ የሚኖሩ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሲመጡ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ስለ ግድቡ የማስገንዘብና ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያደርጉ ስራዎችን ለመስራትም አቅጣጫ ተቀምጧል።

Source: https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=5251