/ሙላት

Published

- 2 min read

/ኢትዮጵያ /የባሕር /በር, /ብሪክስ /አባል

img of /ኢትዮጵያ /የባሕር /በር, /ብሪክስ /አባል

/ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር ተፈራረመች

/ጠቅላይ ሚኒስትር /ዶ/ር. ዐቢይ /አሕመድ እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት /ሙሴ /ቢሂ /አብዲ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ታሪካዊ የሆነ የምግባቢያ ሰነድ ፈርመዋል .

/የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሊላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሰነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖር ግንኙነታቸው ማዕቀፍ የሚሆን ነው .

also checkout on twitterX: https://twitter.com/AbiyAhmedAli/status/1741870681480949851

/የኢትዮጵያ /ስብራት /ጥገና ቀን

/ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ , የባሕር በር አማራጮችን የሚያሰፋ , የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ , የዲፕሎማሲ , የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው .

/እንዲሁም ሰነዱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የሚኖራቸው ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት ነው . ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርሕ እና ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመሥራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያፀና ነው .

/ይህ ሰነድ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው ነው . እንዲሁም ሰነዱ ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ደኅንነት የሚገባትን ሚና እንድትጫወት የተሻለ ዕድል የሚፈጥር ነው .

/የተገኘው ከ፡ https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=5198

/ኢትዮጵያ /በብሪክስ አባልነቷ የጋራ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ትሰራለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

/ኢትዮጵያ በ /ብሪክስ አባልነቷ በአባል ሀገራቱ መካከል የጋራ ተጠቃሚነት እንዲጎለብትና የደቡብ ደቡብ ትብብር እንዲጠናከር እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ .

/ኢትዮጵያ የብሪክስ ሕብረትን በይፋ መቀላቀሏን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል .

/በመግለጫውም ኢትዮጵያ ብሪክስን በይፋ የተቀላቀለችበት የዛሬው ቀን ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ገልጿል .

/ባሳለፍነው ነሐሴ ወር እጅግ ጠቃሚ የሆነውን የአጋርነት ሕብረት ኢትዮጵያ እንድትቀላቀል መወሰኑን መግለጫው አስታውሷል .

/ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የምጣኔ ሀብት እድገት በብሪክስ አባልነት እንድትመረጥ ያስቻላት መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ሀገሪቱ በብሪክስ አባልነቷ የደቡብ ደቡብ ትብብር እንዲጠናከር ያላሰለሰ ጥረት እንደምታደርግ አስታውቋል .

/ከዚህም በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ደህንነት እንዲሰፍን እንዲሁም የጋራ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩሏን ሚና ትጫወታለች ነው ያለው .

/እ/ኤ/አ በ2024 የመጀመሪያው ቀን ኢትዮጵያ በይፋ የብሪክስ አባል መሆኗን ተከትሎ ሀገሪቱ በሕብረቱ የሚኖራትን እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ኮሚቴ መቋቋሙንም መግለጫው ይፋ አድርጓል .

/የተገኘው ከ፡ https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=5199

Congratulations to Ethiopia and it’s people for these accomplishments and wishing you the best in 2024 - mulat.org